Archives August 2024

ፍትሕን የምትሻዋ ነፍስ


በኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ብዙ ህፃናትና ወጣቶች ፆታዊ ጥቃት ደርሶባቸው በማህበራዊ ትስስር ገፅ መነጋገሪያ ሲሆኑ ህዝቡም ስለነሱ ፍትህ ሲጠይቅ ተመልክተናል።

ልጆች ትምህርት ቤት በሂዱበት ጠፍተዋል፣ ወጣቶች በገዛ የትዳር አጋራቸው የአሲድ ጥቃት ሰለባ ሁነዋል፣ ታዳጊዎች በሚማሩባቸው ቦታዎች አብረዋቸው በሚማሩ ወንድ ተማሪዎች ፆታዊ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።

ጥቃት ፃሚዎችም በህግ አግባብ ቅጣት ሲያገኙ አስተውለናል።

በቅርቡ በባህርዳር ከተማ ፍፁም ከሰብዓዊነት ባፈነገጠ መልኩ በአንድ ግለሰብ ምክንያት ህይወቷ ያለፈው የሰባት አመቷ ታዳጊ ሄቨን ጉዳይም የብዙዎችን ልብ የሰበረ አሳዛኝ ክስተት ነው።

ጉዳዩ ብዙዎችን አሳዝኗል፣ የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት አነጋግሯል፣ እናቶች በጭንቀት ፍትህ እያሉ እንዲጠይቁ አድርጓል።

ወንጀሉ የተፈፀመው ሐምሌ 25 ቀን 2015 ሲሆን፤ የምዕራብ ጎጃም ዞን አቃቤ ህግ በቁጥር 063128 በቀን 19/01/2016 በወንጀል ቁጥር 620/3 በመጥቀስ ክስ አቅርቦበታል።

ውሳኔውም ጌትነት ባይህ የተባለው ግለሰብ ሐምሌ 25 ቀን 2015 ከጥዋቱ 3 ሰዓት በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 ውስጥ ህፃን ሄቨን አወት የተባለችውን የ7 ዓመት ህፃን አስገድዶ ከደፈራት በኋላ አንቆ የገደላት መሆኑን በ8ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ መዝገብ ተጣርቶ በመቅረቡ መዝገቡ ተመርምሮ በኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሐ ላይ ተደራራቢ ክስ በመመስረት የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ተከሳሽ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል።

ህፃን ሄቨን ላይ እንዲህ ያለ ዘግናኝ የሆነ ኢ-ሰብአዊ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ የ25 ዓመት እስራት የተፈረደበት ቢሆንም፤ ቅጣቱን ለማቅለል እና ለማስለቀቅ ይግባኝ የተጠየቅበት አካሄድ የህፃኗን ቤተሰቦች የፍትህ ያለ እንዲሉ እና ብዙዎችንም ያስቆጣ ሆኗል፡፡

ህፃን ሄቨን የተፈፀመባት አሰቃቂ መደፈርና ግድያን በተመለከተ የተሰጠው ፍርድ አነስተኛ ነው፣ እንዲሁም በይግባኝ ከእስር ሊወጣ አይገባም በማለት ብዙዎች በዚህ ሰዓት ፍርዱ ይታይልን፣ ፍትህ እንፈልጋለን፣ ፍትህ ለሄቨን የሚል እንቅስቃሴዎችንም እያደረጉ ይገኛሉ።

ጉዳዩን አስመልክቶ የሴቶችና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለችውን ህፃን ሄቨንን በተመለከተ በደረሰው ዘግናኝ የሆነ ኢ-ሰብአዊ ወንጀል የተሰማውን ሀዘን ገልፆ፤ ይህንን አይነት የህፃናት ጥቃት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በፅኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡

በተፈፀመው ወንጀል ዙሪያም የተሰጠውን ዉሳኔ አስመልክቶ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚኬድበት አግባብ ትክክል ባለመሆኑ ከፍትህ አካላት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ እና እንደሚከታተል ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር እንዲሁ ትናንት ባወጣው መግለጫው፤ በባህርዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በኩል ድርጊቱ መፈፀሙን መረጃ እንዳገኘ እና ጉዳዪን ካወቀበት ከጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በቅርበት ሲከታል መቆየቱን አስታውቋል።

ወንጀለኛው የፈፀመው አሰቃቂና ተደራራቢ ወንጀል አሳዛኝና አሰቃቂ ነው ያለው ማህበሩ፤ በተለይ በህፃናት ላይ እንደዚህ ዓይነት ወንጀል ሲፈፀም እጅግ የሚያስከፋና የሚያስቆጣ ነው ሲል ገልጿል፡፡

ፍርድ ቤቱም ወንጀለኛውን በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ብቻ መቅጣቱ እጅግ ያነሰና የግድያ ወንጀሉ ብቻ በራሱ የእድሜ ልክ ወይም የሞት ፍርድ ሊያስቀጣው ሲገባ በ25 አመት ፅኑ እስራት ብቻ ውሳኔ ሰጥቶ ማለፉ ስህተት ነው ብሏል፡፡

የህፃኗ ወላጅ እናትና አባት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለዚህ ጭቃኔ ለተሞላበት ድርጊት አስተማሪ እና ቀጪ ፍትህን እንዲሰጥ እየጠየቁ የሚገኝ ሲሆን፤ ብዙዎችም በማህበራዊ ሚዲያው “ሄቨን ልጄ ናት”፣ “ፍትህ ለህጻን ሄቨን”፣ በህጻን ሄቨን ላይ የተፈጸመውን ዘግናኝና ኢ-ሰብአዊ ወንጀል በፅኑ እናወግዛለን በሚል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ ይገኛል።

በናርዶስ አዳነ

ለቸኮለ ማለዳ! ቅዳሜ ነሐሴ 11/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች

1 የአማራ ክልል መንግሥት ጸጥታ ቢሮ፣ በዛሬው ዕለት ባሕርዳር ከተማ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እንድትመለስ ከነጋዴዎችና የትራንስፖርት ማኅበራት ጋር ከስምምነት ላይ እንደተደረሰ አስታውቋል። ቢሮው፣ የትራንስፖርት ማኅበራትና ድርጅቶች፣ የንግድና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እንዲሁም የመንግሥት ተቋማት ዛሬ መደበኛ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ገልጧል። ትናንት የፋኖ ታጣቂዎች አስተላልፈውታል በተባለው የጥቃት ዛቻ ሳቢያ፣ በከተማዋ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችና የንግድ ድርጅቶችና አገልግሎቶች ተቋርጠው ነበር።

2፤ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር፣ የስንዴ ዱቄትና ሩዝን ጨምሮ በምግብና የግንባታ ዕቃዎች ላይ መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ መታየቱን አስታውቋል፡፡ በተያያዘ፣ ትናንት ብቻ ያላግባብ ዋጋ የጨመሩ 479 የንግድ ድርጅቶች የታሸጉና የ5 የንግድ ድርጅቶች ፍቃድ የታገደ ሲኾን፣ ምርት የደበቁ የንግድ ሦስት ተቋማት ደሞ ንደታሽጉና የስድስቱ ንግድ ፍቃድ እንደታገደ ሚንስቴሩ ገልጧል። በግንባታ ዕቃዎች ላይ ሕገወጥ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 23 የሲሚንቶ፣ 12 የብረት፣ 19 የቆርቆሮና 5 የሚስማር መሸጫ ንግድ ድርጅቶችም ታሽገዋል ተብሏል።

3፤ የአማራና ትግራይ ክልሎች ለሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች መፍትሄ ለማፈላለግ የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ የእስካኹኑ እንቅስቃሴው ስኬታማ መኾኑን መግለጡን፣ የወሎ አማራ የማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ተጨባጭ እውነታውን የካደና በራያ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ የዘነጋ ነው በማለት እንደተቃወመው ዶይቸቨለ ዘግቧል። የማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴው፣ ከአለማጣ ከተማ የተናቀሉ ከ70 ሺሕ በላይ የአማራ ብሄር ተወላጆች እስካሁን ወደቀያቸው መመለስ እንዳልቻሉ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። በራያ አላማጣ ካሉት ከ56 ቀበሌዎች 44ቱ በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ተናግሯል ተብሏል። ዐቢይ ኮሚቴው ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ በራያ አላማጣ ተፈናቃዮችን የመመለሱ ጥረት ስኬታማ ኾኗል በማለት ተናግሮ ነበር።

4፤ አንድ የብሪታንያ ንግድ መርከብ በምጽዋ አቅራቢያ በዓለማቀፍ ባሕር ላይ ሲያልፍ የታጠቁ ሰዎችን የጫነች የኤርትራ ባሕር ኃይል ጀልባ በቅርበት እንደተጠጋችው የተለያዩ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። አንዳንድ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ደሞ፣ በመርከቡ ላይ ከጀልባዋ መሳሪያ እንደተተኮሰበት ጠቅሰዋል። ቀይ ባሕር ላይ የየመን ሁቲዎች በንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ የቆዩም ቢሆንም፣ የኤርትራ የባሕር ኃይል ጀልባ በዓለማቀፍ ባሕር ላይ ወደሚንቀሳቀስ የሌላ አገር የንግድ መርከብ ስትጠጋ ግን የሰሞኑ የመጀመሪያ ክስተት እንደኾነ ተገልጧል። [ዋዜማ]

https://youtube.com/@wolloaddis11?si=kWY7W8qt5igRY-a8

ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ወቅታዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል። የመግለጫው ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ጠላት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን የማፍረስ ህልሙን እና የአማራን ህዝብ በጉስቁልና አዙሪት ዉስጥ ለማቆየት ድፍን አንድ አመት በሚባል ደረጃ በአለች በሌለች ደካማ አቅሙ ማድረግ የሚችለውን ሰይጣናዊ ድርጊት ሲፈፅም ተመልከተነዋል።

በተለይም ጠላት አልቻለም እንጂ ፍርስራሿ ላይ መቆም ከሚፈልጋቸው ቦታዎች ግንባር ቀደሟ የባህር ዳር ከተማ ናት። ሰላም ወዳዱ፣ ሰርቶአዳሪው የባሕር ዳር ነዋሪ፣ የፌደራል የፀጥታ ኃይሎች፣ ለክልሉ እና ለከተማ አስተዳደሩ ጥምር የፀጥታ ኃይል ጥረት እና ጥምረት ከተማችን ባህር ዳር ሰላምና ፀጥታዋ በአንፃራዊነት ተጠብቆ ህዝቡን የሚጠቅሙ ዘርፈ ብዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ሲከናወኑ ከርሟል።

በዚህ ዘወትር የሚበሳጨው እና ቅቱ እውን ባለመሆኑ እረፍት ያጣው ጠላት ከነሀሴ 7/2016 ዓ.ም ም ጀምሮ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቆም አዋጅ አስነግሮ የነበረ ቢሆንም የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ የዚህ እኩይ ተግባር ተባባሪ ሳይሆን በመቅረቱ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውና ሌሎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ሳይስተጓጎሉ ቀጥለዋል። በዚህ የተበሳጨው ጠላት በከተማዋ የተወሰኑ ጥቂት ቦታዎች ጊዜ ሰጭ ፈንጂ በማፈንዳት ከተማውን የማሽበር ስራ ፈጽሟል። ይህም ተደርጎ የጠላት ዕቅድ አልተሳካም።

በእነዚህ ውድቀቶቹ ተስፋ ያስቆረጠው ጠላት ዛሬ ነሀሴ 10 / 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ባስተላለፈው ዛቻና ማስፈራሪያ የከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባጃጅና ታክሲ እንዲያቆሙ ፣ በተወሰነ የከተማው ክፍል የንግድ ድርጅቶችና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በስጋት አገልግሎት እንዳይሰጡ አድርጓል።

በጉዳዩ ላይ ጥምር የፀጥታ ሀይሉና የከተማው አመራር ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት አድርጓል።

ክስተቱ የተፈጠረውም በስጋትና በመደናገር መሆኑን መግባባት ላይ ተደርሷል። በመንግስት በኩል በቂ ዝግጅት ያለ መሆኑንና በከተማችን ምንም የፀጥታ ሰጋት ሊሆን የሚችል ነገር እንደሌለ፣ ለከተማዋና ለነዋሪዎች አስተማማኝ ጥበቃ እየተደረገ እንደሆነ፣ ህግ የማስከበር ዝግጁነቱን በውይይቱ አረጋግጧል።

በነገው ዕለትም ከተማዋ ወደ መደበኛ ሁኔታዋ እንድትመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል።

ስለሆነም በነገው ዕለት የትራንስፖርት ማህበራት እና ድርጅቶች፣ የንግድና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ የመንግስት ተቋማት መደበኛ አገልግሎት መስጠት ይጀመራሉ።

በመሆኑም መላው የከተማችን ነዋሪ በማህበራዊ ሚዲያ በሚለቀቅ የሽብር ወሬና አሳሳች ዜና ሳይደናገር መደበኛ እንቅስቃሴውን ያለምንም ስጋት እንዲቀጥል ከተማ አስተዳደሩ ያሳስባል።

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር

#Tigray

ሁሉንም የፓለቲካ ሃይሎች ያቀፈ መንግስት በአስቸኳይ መመስረት ያስፈጋል ” – ሦስት የፓለቲካ ፓርቲዎች

በትግራይ የሚንቀሳቀሱት ባይቶና፣ ሳወት፣ ናፅነት የፓለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ ፤ ” ሳምንቱን በስርዓቱ ባለቤቶች መካከል በመካሄድ ያለው ህገ-ወጥ እንቃስቃሴና ፍጥጫ ተው መባል ይገባዋል ” ብለዋል።

በህወሓት አመራሮች የተፈጠረው ፍጥጫ ተከትሎ በህዝቡ የሚታየው መረበሽ ያወገዙት ሦስቱ  ተፎካካሪ ፓርቲዎች ” ህግ እየጣሱ በህዝብ ካባ ስም ለመደበቅ የሚደረገው መሯሯጥ እናወግዛለን ” ሲሉ ገልጸዋል።

” ለቡድናዊ ጥቅም ሲባል በህዝብ ቁማር መጫወት መቆም አለበት ”  ያሉት ፓርቲዎቹ ” ደርጅታዊ ይሁን ቡድናዊ ጉዳይ ከህዝብ ህልውና ማጣበቅ እንፀየፈዋለን እንዲቆምም እናሳስባለን ” ብለዋል።  

” የህዝብ ሰላም፣ ህልውናና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ህገ-ወጥ  ፓለቲካዊ ተግባር ሲታ የሚመለከተው የፀጥታ አካልና ህዝብ ያለማዳላት በአስቸኳይ የማስቆም ሃላፍነቱን መወጣት አለበት ” ሲሉም ገልጸዋል።

የተፈጠረው ፓለቲካዊ አለመረጋጋት ዋነኛ መፍትሄው ሁሉም የፓለቲካ ሃይሎች በእኩልነት የሚሳተፉበት መንግስት በአስቸኳይ መመስረት ነውየሚል የመፍትሄ ሀሳብ አቅርበዋል።  ፓርቲዎቹ ሁሉም የፓለቲካ ሃይሎች በእኩልነት የሚሳተፉበት መንግስት በአስቸኳይ የመመስረት ጥሪ በተደጋጋሚ ማቅረባቸውና ግን ሰሚ አለማግኘታቸው  አመልክተዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ፉልሃምን 1 ለ 0 አሸነፈ

***************

ዛሬ በተጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብር ማንቸስተር ዩናይትድ ፉልሃምን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የ2024/2025 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት የተጀመረ ሲሆን ምሽት 4 ሰዓት ላይ ማንቸስተር ዩናይትድ ከፉልሃም ጋር የውደድር ዘመኑን የመጀመሪያ ጨዋታ አድርገዋል፡፡

በዚህም በጨዋታው ማንቸስተር ዩናይትድ ተቀይሮ የገባው ጆሽዋ ዚርኪዝ በ87ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ማሸነፍ ችሏል፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ ነገ ሲቀጥል ኢፕስዊች ከሊቨርፑል፣ አርሰናል ከወልቭስ፣ ኢቨርተን ከብራይተን፣ ኒውካስል ከሳውዝሃምፕተን፣ ዌስትሃም ከአስቶንቪላ እና ኖቲንግሃምፎረስት ከቦርንማውዝ ይጫወታሉ፡፡

ማንቸስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ፉልሃምን 1 ለ 0 አሸነፈ

***************

ዛሬ በተጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብር ማንቸስተር ዩናይትድ ፉልሃምን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የ2024/2025 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት የተጀመረ ሲሆን ምሽት 4 ሰዓት ላይ ማንቸስተር ዩናይትድ ከፉልሃም ጋር የውደድር ዘመኑን የመጀመሪያ ጨዋታ አድርገዋል፡፡

በዚህም በጨዋታው ማንቸስተር ዩናይትድ ተቀይሮ የገባው ጆሽዋ ዚርኪዝ በ87ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ማሸነፍ ችሏል፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ ነገ ሲቀጥል ኢፕስዊች ከሊቨርፑል፣ አርሰናል ከወልቭስ፣ ኢቨርተን ከብራይተን፣ ውካስል ከሳውዝሃምፕተን፣ ዌስትሃም ከአስቶንቪላ እና ኖቲንግሃምፎረስት ከቦርንማውዝ ይጫወታሉ፡፡

#ጉምሩክ🚨

አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች አስወጡ !! ” – ጉምሩክ

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፦

” መንግስት ያወጣውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የብሔራዊ ባንክ ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ መደረጉ ይታወሳል።

በመሆኑንም ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ሰነዱ ተቀባይነት ባገኘበት እለት በነበረው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ  ይደረጋል።

ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ/ም በኋለ ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ደግሞ በአዲሱ የውጭ የምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ  መሰረት በየእለቱ በሚኖረው የምንዛሬ ተመን ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ ይደረጋል።

የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ባለመገንዘብ የተነሳ እቃዎችን በደረቅ ወደብ ያከማቹ አስመጭዎች አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች ሊያስወጡ ይገባል።

የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በመተላለፍ እቃዎችን በደረቅ ወደቦች ያላግባብ በማከማቸት በገበያ ላይ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን። “

#EthiopianCustomsCommission