” አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች አስወጡ !! ” – ጉምሩክ
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፦
” መንግስት ያወጣውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የብሔራዊ ባንክ ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ መደረጉ ይታወሳል።
በመሆኑንም ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ሰነዱ ተቀባይነት ባገኘበት እለት በነበረው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ ይደረጋል።
ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ/ም በኋለ ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ደግሞ በአዲሱ የውጭ የምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ መሰረት በየእለቱ በሚኖረው የምንዛሬ ተመን ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ ይደረጋል።
የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ባለመገንዘብ የተነሳ እቃዎችን በደረቅ ወደብ ያከማቹ አስመጭዎች አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች ሊያስወጡ ይገባል።
የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በመተላለፍ እቃዎችን በደረቅ ወደቦች ያላግባብ በማከማቸት በገበያ ላይ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን። “
#EthiopianCustomsCommission